ቀን 09/02/2014 ዓ.ም ዕለተ ማክሰኞ (ኬላ) ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የድርቢያብር በጎ አድራጎት ማህበር ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ? እንደም አላችሁ? ይህ ሳምንታዊው የበጎ አድራጎት ስራ ዘመቻ ውሎ ዳሰሳችን የተሰኘው አምዳችንን ነው ወደ እናንተ ያደረስነው ከዚያ ሁሉ በፊት ግን በቴክኒካዊ ምክንያት ዘግይተን በማሰራጨታችን ይቅርታ እየጠየቅን ወደ ጥንቅራችን እንሻገር፤ የዛሬው የበጎ ስራ ዘመቻ መርሐግብር ከመንደሮች አውራ ከሆኑት መካከል አብነት መንደር ላይ ስራው ተጧጡፏል ምንድነው ካሉን በሚገርም መልኩ ማህበሩን በፅንፈኝነት የሚጠሉት ወገኖች አፍን የሚያዘጋ፣ ማህበሩ ልማትን አይፈልግም ገለመሌ ገለምሌ ለሚሉት የቤት ሥራ የሆነባቸው አካላት እግረ መንገዳችን ማህበራችን ልማትን ፈላጊ፣ የተረጋጋና ሰላም የሆነ ምቹ ሀገር እንዲፈጠር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እንደሚሰራ ለመግለፅ እንወዳለን፤ ታዲያ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው አብነት መንደር ላይ ያለው ፍሪካስትን በማንጠፍ ማህበሩ የበኩሉን ተወጥቷል፤ ከላይ ለገለፅናቸው ነገሮች ለማሳካት ጣትን ጠቋሚ መሆን ብቻ ሳይሆን በመጀመሪያ ከእኔ ምን ይጠበቃል? ትልቁ መርህ አድርጎ ነውና ማህበሩ የሚንቀሳቀሰው እባካችሁ ለዚህ ማህበር የተሳሳተ አመለካከት ያላችሁ ወገኖቻችን እንግዲህ ምን ይባላል እንደወትሮ እግዜር ልቦና ይስጣችሁ ከማለት በስተቀር፤ የተኛን ለመቀስቀስ፣ የማይሰራን ለማሰራት፣ የሚያወራን ለመግታት በመጀመሪያ እኛው እራሳችን ቅን እንሁን፣ አመለካከታችን የተቃና ይሁን፣ በጎ ህሊና ይኑረን፣ እኔ ምንሰራሁ? እንበል እያለ የማህበሩ አባላትን በሞራልና በምግባር እየመከረ ማኅበረሰቡ ለአካባቢው ዕይታ እንዲሰጥ በማድረግ እንደ ዜጋ ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።